Congratulations እንኳን ደስ አላችሁ

Congratulations እንኳን ደስ አላችሁ
የተማሪዎች ካውንስል መልዕክት
በቅድሚያ በ2016 የኬጂ ተመራቂ ተማሪዎች መፅሄት ላይ የአካዳሚውን ተማሪዎች
ወክዬ ንግግር እንዳደርግ እድሉን ስላገኘሁ በአላህ ስም እያመሰገንኩ የአካዳሚያችን የኬጂ ተመራቂ ተማዎችና ወላጆች እንኳ አደረሳችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ። በመቀጠል በአካዳሚያችን በተማሪዎች ካውንስል የተከናወኑ ተግባራትን እንደሚከተለው አቀርባለሁ
በአልሀበሽ አካዳሚ ያለውን ጥሩ የመማር ማስተማር ልምድ ለማጠናከር እና በስኬት ለማከናወን ከተመሰረቱ አደረጃጀቶች መካከል አንዱ የተማሪዎች ካውንስል ነው፡፡
ካውንስሉ የተመሰረተው ዲሞክራሲያዊ አሰራርን በተከተለ አካሄድ ሁሉንም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን ባሳተፈ የምርጫ ሂደት ነው። ይህም መሆኑ ተማሪዎች የዲሞክራሲያዊ ምርጫን ምንነት እንዲያውቁና በመብቶቻቸው በአግባቡ እንዲጠቀሙ በተግባር ልምድን እንዲቀስሙ እድል የፈጠረ ነው።
የካውንስሉን አወቃቀር በተመለከተ ደግሞ ካውንስሉ የተማሪዎች ተወካዮች ምክር ቤት ያለው ይህ ምክር ቤት መተዳደሪያ ደንብን፣ እቅድንና የሥራ አፈፃፀም ሪፖርትን የማፅደቅ መብት ያለው ነው፡፡
ከዚህ በተጨማሪ በስሩ የትምህርት ዘርፍ፣ የሴቶች ዘርፍ፣ የባህልና የስፖርት ዘርፍ፣ የጤና ጉዳይ ዘርፍ፣ የፍትህ ዘርፍ፣ የበጎ አድራጎት ዘርፍ የሚባሉ በሚኒስቴር መስሪያ ቤት አምሳል የተቀናጀ ንዑሳን አደረጃጀቶች ያሉት ሲሆን በነዚህ ዘርፎች አማካኝነት በርካት ስራዎች አከናውኗል፡፡
ከነዚህም መካከል ዋና ዋናዎቹ
~ በክፍል ተማሪዎች አስተዳደር አማካኝነት የተማሪዎች ሥርዓት እንዲያከብሩ መከታተል
– በመማር ማስተማር ሂደት ላይ የሚነሱ የተማሪዎች ጥያቄዎች ወቅታዊ ምላሽ እንዲያገኙ ማድረግ
~ ተማሪዎች በማስተባበር እና እርዳታ በማሰባሰብ በህይወት ፋና ሆስፒታል በመገኘት ህሙማንን በመጠየቅ፣ የሴቶች ንፅህና መጠበቂያ እና የተለያዩ የትምህርት ቁሳቁስ ገጠር ለሚገኝ ትምህርት ቤት ድጋፍ ማድረግ፣ ለተፈናቀሉ ወገኖቻችን የአልባሳት ድጋፍ ማድረግ፣ ለኢድ ቤተሰብ የሌላቸውን ወገኖቻችንን ተደራሽ ያደረገ ድጋፍ ማድረግ፣ ለተቸገሩ ወገኖቻችን የሚሆን አስቤዛ በፖሊስ ኮሚሽን በኩል ድጋፍ ማድረግ በበጎ አድራጎት ዘርፍ ተከናውኗል
– በአንድ አምስት አደረጃጀት ተማሪዎች እርስ በእርስ እንዲረዳዱና ጤናማ የውድድር መንፈስ እንዲፈጥሩ አድርጓል
– የተለያዩ የስፖርት ቡድኖችን በመፍጠር የስፖርት ውድድርን እንዲካሄድ በማድረግ የተማሪዎችን የአካል ብቃት የማጎልበት ተግባር አከናውኗል
በአጠቃላይ ካውንስሉ የነገ ሐገር ተረካቢ ትውልዶች የአመራር ልምድና የመረዳዳት ፍላጎት እንዲኖራቸው መሰረት የጣለ ተግባር አከናውኗል። ይህም ተግባር በዳበረ መልኩ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በዚህ አጋጣሚ አካዳሚው ያለውን የበርካታ አመት ልምድ በመጠቀም የተማሪዎች ሥነ-ምግባር እንዲሻሻል እና በእውቀት እንዲጎለብቱ ለማስቻል ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ መሆኑን በመገንዘብ ወላጆች ለልጆቻችሁ ለውጥ ከትምህርት ቤቱ ጎን በመቆም የበኩላችሁን እንድታደርጉና እኛ ውጤታማ የነገ ሐገር ተረካቢ ትውልድ እንድሆን በጋር እንድትሰሩ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ።
የተማሪዎች ካውንስል ፕሬዝዳንት
ተማሪ እንዋር ሱሌይማን
2016/2024

Comments

No comments yet. Why don’t you start the discussion?

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *